Gebeya Search

Awlala

3,600 subs • 520 products
Page 21 of 52
(Showing 201 - 210 of 520 products )

2 years ago

2 years ago

ፌስ ሮለርን (face roller) እንዴት ነው መጠቀም ያለብን? ፊትን በቀላሉ ማሳጅ ለማድረግ እና የፊት ቆዳ ጥራትን ለመጠበቅ የሚረዳው ፌስ ሮለር አሁን አሁን በብዛት በሰዎች ዘንድ እየተለመደ መጥቷል። ታዲያ ይህ መሳሪያ የሚሰጠውን ጥቅም በተገቢው ሁኔታ እንድናገኝ አጠቃቀማችን በትክክለኛው መንገድ መሆን አለበት። አንዳንድ ሰዎች አጠቃቀሙን ካለማወቅ የተነሳ ማግኘት ካለባቸው ጥቅም ይልቅ ፊታቸው ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ሰዎች ፌስ ሮለር ሲጠቀሙ ከሚፈጽሟቸው ስህተቶች መካከል ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው። 1. ፌስ ሮለር ከመጠቀማችን በፊት ፊታችን ተገቢውን ወዝ ማግኘት አለበት። ይህም ፊታችንን ማሳጅ በምናደርግበት ወቅት እፍግታ (friction) ተፈጥሮ የፊታችን ቆዳ እንዳይጎዳ ይረዳል። በተጨማሪም ሮለሩ የፊት ቆዳ ቀዳዳዎች እንዲከፈቱ ስለሚረዳ ቅባቱ ወደ ውስጥ ዘልቆ እንዲገባ ይረዳል። 2. ፌስ ሮለር ተገቢውን ውጤት እንዲያሳየን በመደበኝነት መጠቀም ይኖርብናል። ስለዚህ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ፊታችንን በፌስ ሮለር በአግባቡ ማሳጅ እንድናደርግ ይመከራል። 3. የፊታችን የደም ዝውውር እንዲቀላጠፍ እና ወጣት ቆዳ እንድንጎናጸፍ ፊስ ሮለር አጠቃቀማችንን ልብ ማለት አለብን። ሁሌም ፊታችንን ማሳጅ ስናደርግ ከፊታችን ማዕከል ተነስተን ወደውጪ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ መሆን ይኖርበታል። ወደፊት እና ወደ ኋላ እያመላለሱ ማሳጅ ማድረግ አይመከርም። 4. ፌስ ሮለር በምንጠቀምበት ጊዜ ፊታችን ላይ የምናሳርፈው ጫና ተመጣጣኝ መሆን ይጠበቅበታል። በጣምም ጫና ሳናበዛ በጣምም ሳናሳንስ መጠነኛ ጫና ተጠቅሞ ማሳጅ ማድረግ ይመከራል። ሲጠቃለል ፌስ ሮለር ሲጠቀሙ በቅደም ተከተል • ፊትዎን በአግባቡ መታጠብዎን • ፊትዎን በተገቢው ማውዛትዎን • ማሳጅ የሚያደርጉበት መንገድ ትክክል መሆኑን ልብ ይበሉ።

2 years ago

የእጅ ሰዓት መምረጫ መንገዶች የእጅ ሰዓት ዋጋ ከመቶ ብሮች ጀምሮ እስከ መቶ ሺህ ብሮች የዋጋ ልዩነት አላቸው። ጥሩ ሰዓት መርጠው ለመግዛት የሚከተሉትን ነጥቦች በጥንቃቄ ቢያውቁ ይረዳዎታል… ምን አይነት ሰአት ነው የሚፈልጉት? ፦ ልብ ይበሉ የሰዓቶች ስታይል የተለያየ ነው። እርሶም ሰዓት ሲገዙ ለምን አገልግሎት እንደሚፈልጉት በደንብ መረዳት ትክክለኛውን የሰዓት አይነት ለይቶ ለመግዛት ይረዳል። ጥቂት ምሳሌዎች… • ከውሃ እና ከበረዶ አየር ጋር የተያያዘ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ ከሆነ Diving watch የሚባሉትን ሰዓቶች ቢገዙ ይመከራል • ተራራ መውጣት፣ሩጫ ፣ ሳይክል መንዳት ለመሳሰሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሲዎች ደግሞ sport Watches ተመራጭ ናቸው • ለየዕለት እንቅስቃሴዎ ሰአት ከፈለጉ casual የሚባሉትን የሰዓት አይነቶች መግዛት ይመከራል። • ለተለያዩ ፕሮግራሞች እና ዝግጅቶች ዘንጦ ለመታየት formal Watches አይነተኛ ምርጫ ናቸው። መጠንዎን ይወቁ፦ ሰዓት እና የእጅዎ መጠን ካልተጣጣመ ሰዓቱ የፈለገ ውብ ቢሆን ውበቱን ያጎድለዋል። የሰዓቱን ዋነኛ ክፍል (አናቱን) መጠን መቀየር ስለማይቻል ሰዓት ሲገዙ ከእጅዎ መጠን ጋር መጣጣሙን ልብ ማለት ያስፈልጋል።ሰዓቶች አናሎግ ወይም ዲጂታል ሊሆኑ ይችላሉ። የእርስዎ ምርጫ ዬቱ ነው? ሰዓት ሲመርጡ አንዱ በደንብ መለየት ያለብዎት ነጥብ ነው። ሌላው ቀን መቁጠሪያ፣stop watch የመሳሰሉትን አገልግሎቶች ይፈልጉ እንደሆነም ቀድመው መለየት ይጠበቅብዎታል። የሰዓቶች ውሃን የመቋቋም አቅም፣የባትሪ እድሜ ፣ የጊዜ መቁጠሪያዎቹ አቀማመጥ ወዘተ ሰዓት ሲገዙ በደንብ ልብ ሊሏቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው። ሌላው መረሳት የሌለበት ማሰሪያው የተሰራበት ማቴሪያል ነው።


Page 21 of 52
(Showing 201 - 210 of 520 products )