Product
Awlala

1/1
Posted
2 years ago
Description
የእጅ ሰዓት መምረጫ መንገዶች
የእጅ ሰዓት ዋጋ ከመቶ ብሮች ጀምሮ እስከ መቶ ሺህ ብሮች የዋጋ ልዩነት አላቸው። ጥሩ ሰዓት መርጠው ለመግዛት የሚከተሉትን ነጥቦች በጥንቃቄ ቢያውቁ ይረዳዎታል…
ምን አይነት ሰአት ነው የሚፈልጉት? ፦ ልብ ይበሉ የሰዓቶች ስታይል የተለያየ ነው። እርሶም ሰዓት ሲገዙ ለምን አገልግሎት እንደሚፈልጉት በደንብ መረዳት ትክክለኛውን የሰዓት አይነት ለይቶ ለመግዛት ይረዳል።
ጥቂት ምሳሌዎች…
• ከውሃ እና ከበረዶ አየር ጋር የተያያዘ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ ከሆነ Diving watch የሚባሉትን ሰዓቶች ቢገዙ ይመከራል
• ተራራ መውጣት፣ሩጫ ፣ ሳይክል መንዳት ለመሳሰሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሲዎች ደግሞ sport Watches ተመራጭ ናቸው
• ለየዕለት እንቅስቃሴዎ ሰአት ከፈለጉ casual የሚባሉትን የሰዓት አይነቶች መግዛት ይመከራል።
• ለተለያዩ ፕሮግራሞች እና ዝግጅቶች ዘንጦ ለመታየት formal Watches አይነተኛ ምርጫ ናቸው።
መጠንዎን ይወቁ፦ ሰዓት እና የእጅዎ መጠን ካልተጣጣመ ሰዓቱ የፈለገ ውብ ቢሆን ውበቱን ያጎድለዋል። የሰዓቱን ዋነኛ ክፍል (አናቱን) መጠን መቀየር ስለማይቻል ሰዓት ሲገዙ ከእጅዎ መጠን ጋር መጣጣሙን ልብ ማለት ያስፈልጋል።ሰዓቶች አናሎግ ወይም ዲጂታል ሊሆኑ ይችላሉ። የእርስዎ ምርጫ ዬቱ ነው? ሰዓት ሲመርጡ አንዱ በደንብ መለየት ያለብዎት ነጥብ ነው። ሌላው ቀን መቁጠሪያ፣stop watch የመሳሰሉትን አገልግሎቶች ይፈልጉ እንደሆነም ቀድመው መለየት ይጠበቅብዎታል። የሰዓቶች ውሃን የመቋቋም አቅም፣የባትሪ እድሜ ፣ የጊዜ መቁጠሪያዎቹ አቀማመጥ ወዘተ ሰዓት ሲገዙ በደንብ ልብ ሊሏቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው።
ሌላው መረሳት የሌለበት ማሰሪያው የተሰራበት ማቴሪያል ነው።

More from Awlala
Swipe to see more products from this channel